Discover

Topics

Geez Amharic Bible Pro መጽሐፍ ቅዱስ በግዕዝና በአማርኛ

Geez Amharic Bible Pro መጽሐፍ ቅዱስ በግዕዝና በአማርኛ APK

Geez Amharic Bible Pro መጽሐፍ ቅዱስ በግዕዝና በአማርኛ APK

6.1.1 $4.99Goranda Apps

The first complete Ethiopian Orthodox Bible in Geez, Amharic and English

What's Geez Amharic Bible Pro መጽሐፍ ቅዱስ በግዕዝና በአማርኛ APK?

Geez Amharic Bible Pro መጽሐፍ ቅዱስ በግዕዝና በአማርኛ is a app for Android, It's developed by Goranda Apps author.
First released on google play in 5 years ago and latest version released in 3 years ago.
This app has 345 download times on Google play and rated as 4.53 stars with 17 rated times.
This product is an app in Books & Reference category. More infomartion of Geez Amharic Bible Pro መጽሐፍ ቅዱስ በግዕዝና በአማርኛ on google play
በይዘቱ ተሟልቶ በሦስት ቋንቋዎች (በግእዝ፣ በአማርኛና በእንግሊዝኛ) የተዘጋጀ የመጀመሪያው ምሉዕ መጽሐፍ ቅዱስ ነው። ይህ መጽሐፍ ቅዱስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ሥርዓትና ደንብ ጠብቆ የተዘጋጀ ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍ ነው። መጽሐፍ ቅዱሱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት እንዲሁም የቀኖና መጻሕፍት ብላ በ1962 ዓ.ም ያሳተመችውን መጽሐፍ ቃል በቃል ለቅሞ መዝግቧል።

መጽሐፉ ለሃይማኖት አባቶች ለሰባክያነ ወንጌልና ለመምህራን ለመንፈሳዊ ተልዕኮ በሚሰማሩበት ወቅት መጽሐፍ ቅዱስ በእጃቸው መያዝ ሳይኖርባቸው በቀላሉ ቃለ እግዚአብሔርን ለማስተማር ጉልህ አስተዋጽኦ ይኖረዋል:: ምዕመናንም የግዕዙንና የአማርኛውን ትርጉም ምሥጢሩ ሳይዛባ በስልካቸው እንዲጠቀሙ ይረዳል::

የመጽሐፉ ልዩ ባሕርያት
• ሰማንያ አንድ (81) መጻሕፍትን ያካተተ ነው።
• ሙሉ ብሉይና ሐዲስ ኪዳን በኢትዮጵያ ጥንታዊ ቋንቋ በግዕዝ፣ በአማርኛና በእንግሊዘኛ የተዘጋጀ ነው።
• የአማርኛው ትርጉም በጥንታዊው የአባቶቻችን አጻጻፍና አገላለጽ ሃይማኖታዊ ለዛውን ሳይለቅ የተጻፈ ነው።
• የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የምትጠቀምባቸውን የብሉይና የአዲስ ኪዳን የቀኖና መጻሕፍትን ያካተተ ነው።
• ፊደሉና አጻጻፉ በግእዝና በአማርኛ መዛግብተ ቃላት መሠረት ታርሞ የተዘጋጀ ነው።
• የፊደሎችን መጠን በቀላሉ ማስተካከያ መንገድ አለው።
• በቀንና በጨልማ ለማንበብ የራሱ ማስተካከያ ተካቶበታል።
• ማስታወሻ መያዣ፣ ማቅለሚያ፣ ዕልባት ማድረጊያ ተካቶበታል።
• ማጣቀሻዎች በየቁጥሩ የተካተቱ ሲሆን በቀላሉ አንድ ጊዜ ብቻ ጠቅ በማድረግ ገጹን ሳይለቁ ማንበብ ያስችላል።
• በጣም ፈጣንና የፍለጋ ውጤቶችን በማቅለምና በቁጥር የሚያሳይ መፈለጊያ ተካቶበታል።
• የአማርኛ፣ የግእዝና የእንግሊዝኛ ዕትሞችን ጎን ለጎን፣ መስመር በመስመር ፣ ከላይና ከታች አድርገን ለማንበብ ያስችላል።
• የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍትን በአኅጽሮት ወይም በሙሉ ስም ለመዘርዘር ማስተካከያ ተደርጎበታል።
• የፊደል መጠኑን በቀላሉ ማሳነስና ማሳደግ የሚያስችል ማስተካከያ ተካቶበታል።
• የመጽሐፍ ቅዱስ መስመሮችን እንድፍላጎትዎ ማስተካከል ይችላሉ።
• ከዚህ በፊት ያነበቧቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ከዚህ በፊት የተነበቡ በሚለው ስር ያገኟቸዋል።
• የተለያዩ ቋንቋዎችን በመጠቀም የመጽሐፉን ይዘት መተርጎም ይችላሉ።