Discover

Topics

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች APK

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች APK

23.02 FreeApps Show ⇣ Download APK (13.91 MB)

Bible verses. Read. Share. Namely through a new way to read the Bible

What's የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች APK?

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች is a app for Android, It's developed by Apps Show author.
First released on google play in 6 years ago and latest version released in 8 months ago.
This app has 24.6K download times on Google play and rated as 4.53 stars with 60 rated times.
This product is an app in Books & Reference category. More infomartion of የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች on google play
መጽሐፍ ቅዱስ ነብያትና ሓዋሪያት በመንፈስ ተመርተው የጻፉት የክርስቲያኖች እምነት መጽሓፍ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ በብሉይ ኪዳንና በአዲስ ኪዳን ተከፍሎ 66 መጻሕፍት አሉት። ከነዲዩትሮካኖኒካል መጻሕፍትም ጋራ የመጻሕፍት ቁጥር 81 ነው።

የመጽሐፍ ቅዱስ ምንነት

በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተለመደው «ባይብል» የሚለው ቃል ከጥንቱ የኮይነ ግሪክኛ ቋንቋ የተወሰደ ሲሆን ቃሉ የተገኘበት τὰ βιβλία /ታ ቢብሊያ/ የሚለው ሀረግ «መጽሐፍቱ» ወይም «ትንንሽ መጽሐፍት» ተብሎ ሊተረጎም ይችላል። የዚሁም ቃል መነሻ ከግሪኩ ስም ΒύβλΠς /ቢውብሎስ/ (ፓፒሩስ ወይም ቄጠማ፣ የወረቀት ተክል) ሲሆን ይሄ ቃል «ፓፒሩስ» ከተነገደበት ከተማ ጌባል / ቢውብሎስ ስም መጣ።

መጽሐፍ ቅዱስ ለአይሁድና ክርስትና እምነት የእምነት መሰረት የሆኑ ትናንሽ መጽሐፍትን የያዘ አንድ ጥራዝ ነው። በተለምዶ «ብሉይ ኪዳን» በመባል የሚጠራውና በአይሁዳውያን በ24 እና በክርስቲያኖች በ39 መጽሐፍት የሚከፈለው የመጽሐፍ ቅዱስ የመጀመሪያ ክፍል በመጀመሪያ በአብዛኛው የተጻፈው በጥንታዊው የዕብራይስጥ ቋንቋ ሲሆን የተጻፉበት ዘመን ከክርስቶስ ልደት በፊት የተወሰኑ መቶ አመታት ቀደም ብሎ እንደሆነ ይነገራል። እነዚህን መጽሐፍት የጻፉት በወቅቱ የነበሩ የታመኑ አይሁዳውያን ወይም እስራኤላውያን ናቸው። የመጨረሻዎቹን 27 መጻሕፍት በግሪክኛ የጻፏቸው ክርስቲያኖች ሲሆኑ «አዲስ ኪዳን» በመባል በሰፊው ይታወቃሉ። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘው ማስረጃም ሆነ በጣም ጥንታዊ የሆኑት ወጎች እንደሚጠቁሙት እነዚህ 66 መጻህፍት የተጻፉት ግብጽ ኃያል ከነበረችበት ጊዜ አንስቶ ሮም የዓለም ኃያል መንግስት እስከ ነበረችበት ዘመን ባሉት 1600 ዓመታት ውስጥ ነው።

በካቶሊክ ቤተክርስቲያን እምነት መሰረት ከ66ቱ መጽሐፍት በተጨማሪ የተካተቱ የተወሰኑ መጽሐፍት ሲኖሩ፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እነዚህ ተጨማሪ መጻሕፍት (ዲዩቴሮካኖኒካል በመባልም ይታወቃሉ) በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተካተቱትን መጻሕፍት ቁጥር ወደ 81 ያደርሱታል።

ከክርስቶስ ስብከት ቀጥሎ ምዕመናን የሆኑት ለረጅም ዘመን ተጨማሪ መጻሕፍቱን ከነመጽሐፈ ሄኖክና ኩፋሌ ያንብቡ ነበር። የአይሁድ ሰንሄድሪን ረቢዎች በ100 ዓ.ም. አካባቢ በተለይም ረቢ አኪቫ በን ዮሴፍ እነዚህን ተጨማሪ መጻሕፍት ከዕብራይስጥ ቅጂ አጠፉ። እስካሁንም ድረስ በዕብራይስጥ ትርጉም አይታወቁም። አዲስ ኪዳን ከተጻፈ በኋላ፣ ብዙ አጠያያቂ ወንጌሎችና የሌሎች እምነቶች ጽሑፎች ደግሞ ሊሠራጩ ጀመር። ግኖስቲክ የተባለው እምነት ተከታዮች በተለይ ብዙ ሥነ ጽሑፍ ፈጠሩ፣ ይህ ግን ከኦርቶዶክስ ወንጌል የተዛቡ ትምህርቶች ነበር። በ170 ዓ.ም. በክርስትያኖች ዘንድ የቱ መጻሕፍት ትክክለኛ ቅዱሳን መጻሕፍት ናቸው? የሚል ጥያቄ ይነሣ ጀመር። መሊቶ ዘሳርዲስ የተባለ ጳጳስ በዚያን ጊዜ ወደ ኢየሩሳሌም መጻሕፍት ቤት ጉዞ አድርጎ የ ዕብራውያን መጻሕፍት ምን ምን እንደ ነበሩ ዘገበ። ተጨማሪ መጻሕፍቱ ከዚያ በፊት ስለ ጠፉ አልተዘገቡም። ስለዚህ ከዚህ በቀር ምንም ያልተዘረዘሩት ብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ትክክለኛ አይሆኑም የሚል ሀሣብ በሮሜ መንግሥት ክርስቲያኖች ተነሣ። ይህም የአይሁዶች ቀኖና በንቅያ ጉባኤ (317 ዓ.ም.) በሮሜ መንግሥት ለክርስቲያኖች ጸና።