Discover

Topics

የመፅሀፍ ቅዱስ ጥያቄ እና መልስ ጨዋታ

የመፅሀፍ ቅዱስ ጥያቄ እና መልስ ጨዋታ APK

የመፅሀፍ ቅዱስ ጥያቄ እና መልስ ጨዋታ APK

9.8 FreeAbraham Gebeyehu ⇣ Download APK (9.09 MB)

This application teaches the Bible in the form of a question and answer game. It also has a discussion page.

What's የመፅሀፍ ቅዱስ ጥያቄ እና መልስ ጨዋታ APK?

የመፅሀፍ ቅዱስ ጥያቄ እና መልስ ጨዋታ is a app for Android, It's developed by Abraham Gebeyehu author.
First released on google play in 3 years ago and latest version released in 3 years ago.
This app has 0 download times on Google play
This product is an app in Educational category. More infomartion of የመፅሀፍ ቅዱስ ጥያቄ እና መልስ ጨዋታ on google play
የሰው ልጅ በዚህ ምድር ላይ ሲኖር ሁለት አይነት እውቀቶችን ይቀስማል ። እነዚህም መንፈሳዊ እና ሳይንሳዊ እውቀት ናቸው ።
ይህንን መፅሐፍ የተረጎምኩት Bible stories ከሚለው የሞባይል አፕሊኬሽን ነው ።
ይህንን መፅሐፍ ለማዘጋጀት ያነሳሱኝ ነገሮች የሚከተሉት ናቸው ።
አብዛኞቹ ሃይማኖቶች መልካም ስነ ምግባርን ይሰብካሉ ። እነዚህም መንፈሳዊ ፍቅርን ፣ ቤተሰብን ማክበር ፣ አለመዋሸት ፣ ለሰው ክፉ አለመመኘት ፣ አምላካችንን በፍፁም ልባችን ማመን እና መውደድ ፣ ሰውን መውደድ ፣ አለመስረቅ ፣ ሰነፍ አለመሆን ፣ ሰውን አለማማት ፣ ያለንን ማካፈል ፣ ሰውን አለመጉዳት ፣ ዝሙት አለ መስራት ፣ በሃሰት አለመመስከር እና የመሳሰሉት ናቸው ። እነዚህ ነገሮች ደግሞ ህሊናችን የሚነግረን ነገሮች ናቸው ።
እዚህ ላይ የክቡር ከበደ ሚካኤልን ግጥም ማስታወስ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ይህም

ፅድቅና ኩነኔ ቢኖርም ባይኖርም
ከክፋት ደግነት ሳይሻል አይቀርም

መፅሀፍ ቅዱስ ከላይ የጠቀስናቸውን ነገሮች ያስተምረናል ። ክርስቲያኖች መፅሐፍ ቅዱስን በየእለቱ ማንበብ እና በህይወታቸውም መተግበር አለባቸው ። ወላጆች ልጆቻቸውን መፅሀፍ ቅዱስን እንዲያነቡ እና እንዲተገብሩ ማበረታት አለባቸው ። ነገር ግን አብዛኞቻችን ይህንን አናደርግም ።
በተጨማሪም በሀገራችን ለልጆች በሚመች መልኩ ከመፅሃፍ ቅዱስ ተወጣጥቶ የተፃፉ ብዙ መፅሀፍት የሉም ።

አሁን ባለንበት ዘመን ልጆችን ወደተሳሳተ መንገድ የሚመሩ ነገሮች በዝተዋል ።
ስለዚህ ስለ መንፈሳዊ ህይወት እና ስለ መልካም ስነምግባር ልጆችን ማስተማር በዚህ ግዜ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው ።
ይህ አፕሊኬሽን የተዘጋጀው በጥያቄ እና መልስ ጨዋታ መልክ ስለሆነ የተዘጋጀው አዝናኝ ነው ።

አንድ ጥያቄ ስትመልሱ አስር ነጥብ ታገኛላችሁ ። አንድ ጥያቄ ስትሳሳቱ ሁለት ነጥብ ይቀነስባችሃል ። ጥያቄውን መመለስ ካልፈለጋችሁ "ይህ ጥያቄ ይለፈኝ ።" የሚለውን መምረጥ ትችላላችሁ ።
ሁሉም ጥያቄዎች ምርጫ ናቸው ።
ጥሩ ነጥብ ለማግኘት "የመፅሀፍ ቅዱስ ትምህርቶች ለሁሉም" የሚለውን አፕሊኬሽን ከ Google play store ላይ አውርዳችሁ ማንበብ ትችላላችሁ ። ወይንም መፅሐፍ ቅዱስን ማንበብ ትችላላችሁ ።

ዋናው የዚህ አፕሊኬሽን አላማ ልጆች ስለ መፅሐፍ ቅዱስ እና ስነ ምግባር አጠቃላይ እውቀት እንዲኖራቸው ለማድረግ ነው ። በተጨማሪም ልጆች መፅሃፍ ቅዱስን እንዲያነቡ ለማነሳሳት ይጠቅማል ።

ውድ አንባቢያ ሆይ መፅሐፍ ቅዱስ በህይወትህ ከሚያስፈልጉህ ዋነኛው እና አንደኛው ነገር ነው ። ያለ እሱ ህይወት አስቸጋሪ ነው ። ለልጅህም ከምታወርሰው ትልቁ ስጦታ የመፅሀፍ ቅዱስን የሚያክል የለም ።
ይህንን አፕሊኬሽን ሲጠቀሙ ጥሩ የኢንተርኔት ኮኔክሽን ያስፈልጋል ።
ይህንን አፕሊኬሽን ለመጀመሪያ ግዜ ሲከፍቱ ስሞትን ማስገባት አለቦት ።

ይህ አፕሊኬሽን የመወያያ ገፅ አለው ።

ይህ አፕሊኬሽን update ሳያስፈልገው ተጨማሪ መረጃዎችን ማግኘት ስለሚያስችል ከግዜ ወደ ግዜ አዳዲስ የተጨመሩ ነገሮች ሊኖሩት ስለሚችል በየተወሰነ ቀናት ኢንተርኔት ኮኔክሽን ከፍተን ከዚያ አፕሊኬሽኑን መክፈት ይመከራል ። ለምሳሌ የተጨመረ ክፍል ካለ ኢንተርኔት ከፍታችሁ ይህን የተጨመረውን ክፍል አፕሊኬሽኑ ላይ ማግኘት ትችላላችሁ ።
ይህንን አፕሊኬሽን ለመጀመሪያ ግዜ ሲከፍቱ ስሞትን ማስገባት አለቦት ።