Discover

Topics

የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ First Aid

የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ First Aid APK

የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ First Aid APK

4.21 FreeOromNet Software and Application Development ⇣ Download APK (10.01 MB)

Emergency & First Aid Essentials የድንገተኛ አደጋና የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ መሠረታዊ Info Amharic

What's የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ First Aid APK?

የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ First Aid is a app for Android, It's developed by OromNet Software and Application Development author.
First released on google play in 8 years ago and latest version released in 8 months ago.
This app has 27.2K download times on Google play and rated as 4.22 stars with 115 rated times.
This product is an app in Medical category. More infomartion of የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ First Aid on google play
የድንገተኛ አደጋና የመጀመሪያ የህክምና እርዳታ
Emergency and First Aid Essentials Android App

ይህ የድንገተኛ አደጋና የመጀመሪያ የህክምና እርዳታ የተሰኘ የአንድሮይድ ሞባይል አፕሊኬሽን በኛ ወይም በአከባቢያችን ሳናስበዉ ሊከሰት የሚችልን ድንገተኛ አደጋዎች በተመለከተና በአደጋዉ ጊዜ ምን ማድረግ እንዳለብን መሠረታዊ ግንዛቤ የሚያስጨብጥ አፕሊኬሽን ነዉ፡፡ የየእለት ኑሮ ዉስጥ ለተለያዩ ድንገተኛ አደጋዎች ልንጋለጥ እንችላለን፡፡ በትራንስፖርት ላይ ወደ ስራም ሆነ ሌላ ቦታ ስንሄድ ድንገተኛ አደጋ ቢያጋጥመን ወይም አደጋ የደረሰባቸዉን ሰዎች በመንገድ ላይ ብናይ ምን ማድረግና እንዴት መርዳት እንዳለብን ከዚህ ሞባይል አፕሊኬሽን መሠረታዊ ግንዛቤ ያገኛሉ፡፡

አፕሊኬሽኑ በአደጋ ጊዜም ሆነ በፊት ምን ማድረግ እንዳለብን እንዲሁም እንዴት ለአደጋዉ መፍትሄ ልናበጅለት እንደምንችል ያስተምረናል፡፡ በተጨማሪም አንድ አደጋ የደረሰበትን ሰዉ ሲያጋጥመን ለዚህ ሰዉዮ ምን አይነት እርዳታ እናደርግለታለን? እንዴት እንረዳዋለን የሚሉትን ጥያቄዎች በከፊል መልስ ከዚህ የድንገተኛ አደጋና የመጀመሪያ የህክምና እርዳታ አሰጣጥ አፕሊኬሽናችን ታገኙታላችሁ ፡፡

በዚህ አፕሊኬሽን ያካተትናቸዉ ርዕሶች፡-የመኪና አደጋ ሲደርስ፣ የእሳት አደጋ፣ የእሳት ማጥፊያ መሳሪያ አጠቃቀም፣ የመጀመሪያ የህክምና እርዳታ፣ መድማት፣ ነስር፣ ድንገተኛ የስኳር ህመም፣ እስትሮክ፣ ቃጠሎ፣ ጭንቀት፣ በኤሌክትሪክ ለተያዘ፣ በጥይት መመታት፣ የጭንቅላት ግጭት ወይም ጉዳት፣ ማንቀጥቀጥ ወይም የሚጥል በሽታ፣ የአስም ሕመም፣ የልብ ህመም የተሰኙት አደጋዎች ሲከሰቱ እንዴት እርዳታ መስጠት እንዳለብን ያብራራል፡፡

አስተያየት ካላቹ በኢ-ሜይል [email protected] ላኩልን፡፡ አፕሊኬሽኑ ወደፊት ተጨማሪ መረጃዎችን አካቶ በየጊዜው ይሻሻላል፡፡ የተጠቃሚዎች አስተያየት እና ፍላጎትን ባማከለ መልኩ አፕሊኬሽኑን ለማሻሻል እንተጋለን፡፡ እባክዎን አስተያየታችሁ አይለየን።

ልብ ይበሉ! ይህ አፕሊኬሽን በማንበብ ጥሩ ግንዛቤ ታገኛላችሁ፤ ንባብ ብቻውን በቂ አይደለም፡፡ በተጨማሪም የኢትዮጲያ ቀይ መስቀል ማህበር እንዲሁም ሌሎች ድርጅቶች የሚሰጡትን የመጀመሪያ የህክምና እርዳታ ስልጠና እንድትወስዱ እናሳስባለን፡፡ ምክንያቱም እያንዳንዱን ለአደጋ የሚሰጥ እርዳታ በተግባር የታገዘ ስልጠ ሲጨመርበት የተሸለ ዉጤት ያስገኛል፡፡ ለራስም ሆነ ለቤተሰብ እንዲሁም ለማህበረሰብም ስለ እርዳታ አሰጣጥ ማወቅ ለሁሉም ይጠቅማል፡፡

አንዴ ሞባይላችን ላይ ከጫንን ቡኋላ በኦፍላይን ልንጠቀም እንችላለን፡፡ ለአጠቃቀም ምቹ ስለሆነ ሞባይልዎ ላይ ጭነዉ ይጠቀሙበት፡፡

አፕሊኬሽናችንን ስለተጠቀሙ እናመሰግናለን!


Please rate our app in the Google Play store.

Thank you for downloading,

ኦሮምኔት የሶፍትዌር እና የሞባይል አፕልኬሽን ዲቬሎፕመንት PLC ነቀምቴ ኢትዮጵያ
OROMNET Software and Application Development PLC, Nekemtie, Ethiopia