Discover

Topics

እርግዝናና ወሊድ Pregnancy in Amharic መረጃ

እርግዝናና ወሊድ Pregnancy in Amharic መረጃ APK

እርግዝናና ወሊድ Pregnancy in Amharic መረጃ APK

4.63 FreeOromNet Software and Application Development ⇣ Download APK (11.20 MB)

እርግዝና እና ወሊድ Pregnancy and Birth Useful Info ሙሉ መረጃ in Amharic Ethiopian

What's እርግዝናና ወሊድ Pregnancy in Amharic መረጃ APK?

እርግዝናና ወሊድ Pregnancy in Amharic መረጃ is a app for Android, It's developed by OromNet Software and Application Development author.
First released on google play in 8 years ago and latest version released in 8 months ago.
This app has 96.2K download times on Google play and rated as 4.55 stars with 343 rated times.
This product is an app in Health & Fitness category. More infomartion of እርግዝናና ወሊድ Pregnancy in Amharic መረጃ on google play
እርግዝናና ወሊድ Pregnancy ሙሉ መረጃ

ይህ እርግዝና እና ወሊድ የተሰኘ የሞባይል አፕሊኬሽን ከቅድመ እርግዝና እስከ ድህረ ወሊድ ያለዉን እዉቀት አካቶ የያዘ ነዉ ፡፡በዚህ የሞባይል አፕሊኬሽን እርግዝናን በተመለከተ የሚደረግ ጥንቃቄና የእርግዝናን ሂደት በየሳምንት (እንደግመዋለን የየሳምንቱን የእርግዝና ሁኔታ) መረጃዎችን ያገኙበታል፡፡ እግርዝናዬ የሞባይል አፕሊኬሽን ለማንኛዉም ጥንዶች የሚሆንና ከማርገዝ በፊትም ሆነ ከእርግዝና ቡኋላ ሊከሰት የሚችልን አደገኛ ክስተቶችን ለመከላከልና ቀድሞዉ እንዲዘጋጁበት ይረዳቸዋል፡፡

አብዛኛዉ ጊዜ አዲስ ተጋቢዎች የመጀመሪያ እርግዝና ላይ ብዙ ያልጠበቁት ነገሮች ሲያጋጥማቸዉ በጣም ይደናገጣሉ፤ ስለዚህ ይህ አፕሊኬሽን ከዶክተር ክትትል ጋር ታጅቦ ብዙ ሊጠቀሙበት ያስችላቸዋል፡፡

አቶ ባል! ባለቤትዎ አርግዘዋል? እንኳን ደስ አልዎት! እንግዲያዉስ ለውድ ባለቤትዎ ሊያደርጉላት የሚችሉት ጥንቃቄዎችና በእርግዝና ጊዜ ሊታይባት የሚችሉትን ያልተለመዱ ባሕሪያትን በዚህ አፕሊኬሽን በመታገዝ ቀድሞ በማወቅ እንክብካቤና እርዳታ ሊያደርጉላት እንዲችሉ ተደርጎ የተዘጋጀ ስለሆነ በቀላሉ መንገድ ሞባይሎት ላይ ጭነዉ ሊጠቀሙበት ይችላሉ፡፡

በዚህ አፕሊኬሽን ያካተትናቸዉ ርዕሶች፡-
-የጽንስ አጀማመር፣ ለማርገዝ ወሳኝ ወቅት፣ የእርግዝና ግንኙነት፣ የወር አበባ መዘግየት እና መጥፋት፣ እርግዝናን ማረጋገጥ፣ የእርግዝና ምልክቶች፣ ማርገዝ አለመቻል (መካንነት)፣ የሴቶች መካንነት፣ የወንዶች መካንነት፣ በእርግዝና ወቅት ስለሚያጋጥሙ አደገኛ የጤና ምልክቶችና መፍትሔዎች፣ በቅድመ ወሊድ ስለሚሰጡ የሕክምና ትትሎች መረጃዎች፣ ወላጆች የቅድመ ወሊድ ክትትል በማድረግ የሚያገኙት ጥቅም፣ ጤናማ ፅንስና የተመጣጠነ ምግብ፣ እናትና ልጅ በእርግዝና ወቅት ፣ የመጀመሪያዎቹ ሦስት ወራት ፣ ከ4ኛዉ -6ኛዉ ወራት ፣ ከ7ኛዉ -9ኛዉ ወራት ፣ እርግዝናና ኤች.አይ.ቪ. ፣ ከወሊድ በኋላ፣ ከወሊድ በኋላ ወሲብ፣ የአውሮፕላን በረራ፣ የተፈጥሮ ወሊድ እና የሲ-ሴክሽን (ቀዶ ጥገና) ወሊድ፣ ከወሊድ በኋላ ክብደትን መቀነስ፣ ህጻኑን መንከባከብ፣ እንቅልፍ ከወሊድ በኋላ .... የተሰኙትን ርዕሶች እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን መረጃ ዘርዘር አድርጎ ይዟል፡፡

በእነዚህ መረጃዎች ላይ መቶ በመቶ ጥገኛ መሆንም የለብንም፡፡ እነዚህ መረጃዎች የሀኪምን ምክር እና የህክምና ባለሞያዎችን ምክር አይተኩም ወይም አማራጭ አይደሉም፡፡ መረጃዎቹ የተሟሉ ወይም ሙሉ በሙሉ መልስ የሚሰጡ ወይም አጠቃሎ የያዙ አይደሉም፡፡

እነዚህ መረጃዎችን ብቻ ተጠቅመን ምንም አይነት የህክምና እገዛ ወይም ምርመራ ማድረግ የለብንም፡፡ ከህክምና ጋር በተያያዘ ጥያቄ ካላችሁ ሀኪምን ማማከር ምንግዜም ቅድሚያ ሊሰጠዉ ይገባል፡፡ በአፕሊኬሽኑ ላይ ያለዉን መረጃ ብቻ በማንበብ የሀኪምን ምክር እና አስተያየት ማጣጣል የለብንም፡፡

አፕሊኬሽኑ ወደፊት ተጨማሪ መረጃዎችን አካቶ በየጊዜው ይሻሻላል፡፡ የተጠቃሚዎች አስተያየት እና ፍላጎትን ባማከለ መልኩ አፕሊኬሽኑን ለማሻሻል እንተጋለን፡፡ አስተያየት ካላቹ በኢ-ሜይል [email protected] ላኩልን፡፡ እባክዎን አስተያየታችሁ አይለየን።

አንዴ ዳወንሎድ ከጫንን ቡኋል FREE offline በ ኦፍላይን ልንጠቀም እንችላለን፡፡

ለአጠቃቀም ምቹ ስለሆነ ሞባይልዎ ላይ ጭነዉ ይጠቀሙበት፡፡

አፕሊኬሽናችንን ስለተጠቀሙ እናመሰግናለን!

ኦሮምኔት የሶፍትዌር እና የሞባይል አፕልኬሽን ዲቬሎፕመንት PLC ነቀምቴ ኢትዮጵያ
OROMNET Software and Application Development, Nekemte, Ethiopia